We're closely monitoring the weather forecast for Sunday’s NYRR Fred Lebow Half Marathon. Please check our website and social media for up-to-date information leading up to the race.

Rules of Competition-Amharic

 

የውድድር ሕጎችና

የኒው ዮርክ ጎዳና ሯጮች (“NYRR”) ዝግጅት በዩኤስኤ የመምና ሜዳ (“USATF”) ሕጎችና ደንቦች የሚዘጋጅና የሚመራ ነው፡፡ አዲስ ገቢዎች የከተማው፣ የስቴቱና የፌደራል ህጎች (የኒው ዮርክ መናፋሻዎችና የመዝናኛ ሕግና ደንቦችን ጨምሮ) የሚተገበሩባቸው ይሆናል፡፡

ደህንነት

የዝግጅቱ አዘጋጆች፡- ሁሉም ተሳታፊዎች የዝግጅቱ አዘጋጆች፣ NYRR ሰራተኛ እና/ወይም በጎ ፈቃደኞች የሚሰጧቸውን መመሪያዎች መከተል አለባቸው፡፡ ተሳታፊዎች በዝግጅቱ አዘጋጆች፣ በህክምና ሰራተኞች ወይም የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፖሊስ ባልደረቦችን ጨምሮ በማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን እንዲያቆሙ ከተጠየቁ ትእዛዙን መቀበል አለባቸው፡፡

ስፖርታዊ ጨዋነት፡- ማንኛውም ተሳታፊ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ ከሆነ/ች ወይም ነውረኛ ባህሪ ካሳየ ወይም ቋንቋ ከተጠቀመ በዝግጅቱ አዘጋጆች፣ NYRR ሰራተኞች እና/ወይም በጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ባህሪ በዝግጅቱ ማመልከቻ ግዜ ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ መስጠትን ይጨምራል፡፡

የተሳታፊዎች መግቢያና የውድድር ቁጥር (ተለጣፊ ቁጥር)

የዝግጅት ማመልከቻ፡- ሁሉም ተሳታፊዎች ለዝግጅቱ ማመልከቻ በሚሞሉ ግዜ እድሜ፣ ጾታና የድንገተኛ ግዜ ተጠሪን ጨምሮ ትክክለኛ መረጃን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዝግጅቱ ከተጀመረ በኋላ ተሳታፊዎች ተያያዥ ቡድኖችን መቀየር አይችሉም፡፡ በቡድን የሚተዳደሩበት ሕጎች በ NYRR ድረገጽ https://www.nyrr.org/charities-clubs-and-community/local-clubs/guideline... ላይ ይገኛል፡፡

የውድድር ቁጥር/ተለጣፊ ቁጥር፡- የውድድር ቁጥርዎን የሚያሳየው ይፋዊ ተለጣፊ ቁጥርዎ ሁል ግዜ በግልጽ መታየትና ከውጭ የለበሱት ልብስ ላይ በፊለፊት መታየት ይኖርበታል፡፡ የግዜ መቁጠሪያ መሳሪያ (ቢ-ታግ) ከኋላዎ ባለው ተለጣፊ ቁጥሩ ላይ መያያዝ ይኖርበታል፡፡ ትክክለኛ ግዜውን እርግጠኛ ለመሆን ተለጣፊ ቁጥሩን አይጠፉ ወይም አያጨማዱ ወይም በጃኬት፣ በሯጭ ቀበቶ፣ በውሀ ጠርሙስ ወይም በሌላ ነገር አይሸፍኑት፡፡ ተለጣፊ ቁጥሩ በአግባቡ ሳይያያዝና ሳይታይ በሩጫው ላይ የሚሳተፉ የማጠናቀቂያ ግዜአቸውና የተለየ ግዜ ሪከርድ ስለማይኖራቸው በውጤት ዝርዝሩ ላይ ላይገለጹ ይችላሉ እና/ወይም ውጤቱን ለማጠናቀቃቸው እውቅና ላይሰጣቸው ይችላል፡፡ በሩጫው ግዜ ተለጣፊ ቁጥርዎ ከጠፉቦት፣ ለዝግጅቱ አዘጋጆች ከሩጫው በኋላ በፍጥነት ያሳውቁ፡፡ የውድድር እውቅና ከመጀመሪያው ሰአትዎ ከተመዘገበ ውድድሩን ማጠናቀቁ ከተረጋገጠ በኋላ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ማስተላለፍ አይፈቀድም፡- በ NYRR ለተሳታፊ ተለይቶ ከተሰጠው የውድድር ቁጥሮችና ይፋዊ የተሳትፎ ተለጣፊ ቁጥሮች ማስተላለፍ፣ ማባዛት ወይም በማንኛውም አይነት መቀየር አይቻልም፡፡ እነዚህን ማድረግ አይችሉም፡- 1) ለሌላ ሰው ቁጥርዎትን ወይም ታግዎትን መስጠት ወይም መሸጥ አይችሉም፣ 2) ከሌላ ሰው ቁጥር ወይም ታግ መቀበል ወይም መግዛት፣ 3) ቁጥሮትን ወይም ተለጣፊ ቁጥርዎትን ለማንኛውም ተግባር መቀየር፣ መቅዳት ወይም ሌላ ዳግም ምርት/እንዲባዛ ማድረግ (ወይም ሌሎች እንዲያደርጉት መፍቀድ)፣ እና/ወይም 4) ይፋዊ ባልሆነ የመወዳደሪያ ቁጥር ወይም ተለጣፊ ቁጥር መሳተፍ (ማለትም በ NYRR ባልተሰጠ ቁጥር ወይም ተለጣፊ ቁጥር)፡፡ አስመስሎ የመስራት ሙከራ የተከለከለና እነዚህን ህጎች ተላልፎ የተገኘ ግለሰብ ቅጣት የሚጣልበት የሚጨምር ነገር ግን በዚህ ብቻ ሳይወሰን ከውድድር ውጭ ማድረግና በተከታታይ የ NYRR ዝግጅቶች ሊያግድ ይችላል፡፡

መጀመር

ማስጀመሪያ ቦታ፡- ተሳታፊዎች ወደ ተሰየሙበት ቦታ የመሄድ ኃላፊነቱ የራሳቸው ነው፣ በሚመርጡት ቦታ መዝጊየ ሰአቱ ከመድረሱ በፊት ወደ ቦታው መድረስ ይኖብዎታል፡፡ ሯጮች ዝቅ ብለው ወደሚሮጡ ቦታ ተመልሰው መሄድ ሊኖርባቸው ይችላል ነገር ግን ወደ ፈጣኑ ቦታ ወደፊት መሄድ አይችሉም፡፡ መከላከያዎቹን ዘሎ ከሄደ ወይም ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ከገባ ከውድድሩ ውጭ ሊደረግ ይችላል፡፡ ለተሳታፊዎች ደህንነት ሲባል ቦታው አንዴ ከተዘጋ፣ ያረፈዱ ተሳታፊዎች በመጨረሻው ቦታ ላይ ሪፖርት ማድረግ አለባቸው፡፡ NYRR ቦታ ያዦች አርፍደው የመጡ ሰዎችን ለደህንነት ሲባል ሊያግዷቸው ይችላሉ፡፡ ወደ ቦታው በሚገቡ ግዜ የዝግጅቱን አዘጋጆች መመሪያ ይከተሉ፡፡ በቦታው ላይ የሚሸና ወይም የሚጸዳዳ ከውድድር ውጭ ሊደረግ እና/ወይም ከ NYRR ዝግጅቶች ሊታገድ ይችላል፡፡

ሩጫ መጀመር፡- እስካልተገለጸ ድረስ ውድድሩ የሚጀምረው በጥሩንባ ነው፡፡ ሁሉም ተሳታፊዎች ውድድሩ ሲጀመር መሆን ያለባቸው ከመጀመሪያው መስመር ኋላ ሲሆን የውድድሩን አስጀማሪ መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ውድድሩ እንዲጀመር የሚመከር ከሆነ፣ ቦታው የተለመደ ክፍተት የሚኖረው ሲሆን ኤ ቦታ በመጀመሪው ጥሩንባ ይጀምራል፣ በመከተልም በተጨማሪ የማስጀመሪያ ጥሩንባ ጩኸት እያንዳንዱ ቀጣይ ይጀምራል፡፡

ግዜ መጠበቅ

ይፋዊ ግዜአት፡- ይፋዊ (የተጣራ) ማጠናቀቂያ ግዜዎት በግዜ መጠበቂያ ሲስተሙ የሚቀዳ ሲሆን ይህም የመጀመሪያውን መስመር ካለፉና የመጨረሻውን መስመር እስከሚያልፉ ድረስ ነው፡፡ ይህ ግዜ ያጠናቀቁትን ዝርዝር የሚይዝና ከላይ ካሉት አሸናፊዎች በስተቀር በእድሜ-መድቦ ለአሸናፊዎች ለመሸለም የሚያስችል ሲሆን በመሳሪያ ግዜ (ከማስጀመሪያው ጥሩንባ እስከ ሯጩ የመጨረሻውን መስመር እስከሚያፍበት ድረስ) የሚወሰን ነው፡፡ የሜዳው መጠን የመጀመሪያው መክፈቻ ረጅም ካልሆነ በስተቀር የማስጀመሪያ ግዜ ሪቫኑ የመጨረሻው ቦታ ላይ ሩጫው ሲጀመር የሚነሳ ይሆናል፡፡ መጀመሪያው ከተዘጋ በኋላ፣ የተጣራው ግዜ የማይያዝና ግዜው የሚሰላውም የማስጀመሪያ ጥሩንባው ከጮኸ በኋላ ነው፡፡ ሯጩ የግዜ መጠበቂያ ሪቫኑ ከተነሳ በኋላ ከጀመረ፣ የመጀመሪያ ግዜ አይጨመርለትም፡፡

መሮጫ መንገዱ

የመሮጫ መንገድ ምልክት፡- NYRR ዝግጅቶች (ከህጻናት ውድድሮች በስተቀር) የሚካሄደው በ USATF በተመሰከረለት የመሮጫ መንገድ ነው፡፡ ተሳታፊዎች ሁልግዜም በመሮጫ መንገዱ ላይ መሆን አለባቸው፡፡ የመሮጫ መንገዱ በመከለያ፣ በትራፊክ ኮኖች፣ በመግለጫዎች እና/ወይም በሌሎች ምልክቶች የተደረገበት ነው፡፡ ተሳታፊዎች የመሮጫ መንገዱ፣ አቅጣጫዎች፣ ተቋሞች ጋር ግንኙነት ያላቸውን የዝግጅቱን ምልክቶች መለየትና መረዳት ያለባቸው ሲሆን የመሮጫ መንገዱ ሰራተኞችና የዝግጅቱ አዘጋጆች የሚሰጧቸውን መመሪያዎች መከተል አለባቸው፡፡ ይህን አለማድረግ ከውድድሩ ውጭ መሆንን ሊያስከትል ይችላል፡፡

የመሮጫ መንገዱን ማጠናቀቅ፡- ሁሉንም መንገድ ካላጠናቀቁ፣ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡ በማረጋገጫ ቦታው ላይ የሌለ ወይም ወጥ ያልሆነ ግዜ ያለው ተሳታፊ ሁኔታው እንዲታይ ይደረግና ከውድድር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ከመሮጫ መንገዱ መውጣት ካለብዎት፣ ወዲያውኑ በወጡበት መመለስ ይኖርብዎታል፡፡ ቦታ ለማግኘት ወይም ሌላ ተወዳዳሪን ለመርዳት ብሎ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተሳታፊ ከመሮጫ መንገዱ ወጥቶ መመለስ አይችልም፡፡

ድጋፍ፡- ካልተፈቀደለት ተመልካች ወይም ያልተመዘገበ ተሳታፊ በመሮጫ መንገዱ ላይ መገኘት እንዲሁም ድጋፍ ማድረግ አይፈቀድለትም፡፡ ከተፈቀደለት የህክምና ባለሙያ ውጭ እገዛ ያገኘ ተሳታፊ ከውድድር ውጭ ሊደረግ ይችላል፡፡

የግዜ ገደብ፡- ለደህንነት ሲባል፣ እንዲሁም በተያዘው እቅድ መሰረት መንገዶችና መናፈሻዎች እንደገና እንዲከፈቱ፣ በእያንዳንዱ የሩጫ ገጽ መሰረት የሩጫ ማጠናቀቂያ ሰአት መሰረት የመሮጫ መንገዱ ለሁሉም ተሳታፊዎች ክፍት ይሆናል፡፡ ከመዝጊያው ግዜ በፊት ሩጫውን መጨረስ ያልቻሉ ሯጮች የፈሳሽ ጣቢያና ሌሎች ለሩጫ የሚመቹ ድጋፎች ላይኖሩ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ በኒው ዮርክ ከተማ ጎዳናዎች የሚሮጡ ተሳታፊዎች በዝግጅቱ አዘጋጆች ወደ ዳር እንዲወጡ ወይም በአውቶቢስ እንዲሳፈሩ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ በአውቶቢስ የተሳፈሩ ተሳታፊዎች የመጨረሻውን መስመር አያልፉም፡፡

ማጠናቀቂያው

ዘግይተው የሚመጡ ተሳታፊዎች እውቅና እንዳለው አጠናቃቂ ግዜ ለመያዝና ለመመዝገብ ዋስትና ላይኖራቸው ይችላል፤ በመሆኑም በውድድሩ ላይ እውቅና እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ የውድድሩን ውጤት ሰጪ ቡድን ያናግሩ፡፡

የተከለከሉ ቁሳቁሶች

የሚከተሉት ቁሶች በሁሉም NYRR ዝግጅቶችና ውድድሮች ላይ ክልክል ናቸው፡-

• የጦር መሳሪያ፣ ጩቤዎች፣ ገጀራ፣ ወዘተ ጨምሮ ማንኛውም አይነት መሳሪያ፡፡  

• አደገኛ ቁሶች ወይም መዶሻ፣ መጋዝ፣ ስለት ያላቸው ነገሮች፣ ዣንጥላ፣ ዘንግ፣ ዱላ፣ ወዘተ ጨምሮ “ጣምራ-ጥቅም” ያላቸው ቁሶች አደገኛ እንደሆኑ ይታሰባል፡፡  

• ተቀጣጣይ ፈሳሾች፣ አርሶል፣ ነዳጅ፣ እርችት፣ መርዛማ ኬሚካሎች፣ ፈንጂዎች 

• ትልቅ ጥቅል፣ ማቀዝቀዣዎች፣ ድንኳኖችና ጊዜአዊ መጠለያ  

• አልጋ ልብስ፣ መተኛ ቦርሳ/ስሊፒንግ ባግና ትልቅ ብርድልብስ ወይም 

• የአልኮል መጠጦችና ማንኛውም አይነት ህገወጥ እጾች

• ስም የለሽ የአየር መሳሪያዎች፣ ድሮኖች፣ የቅኝት ባሉኖች፣ ፎቶግራፍ አንሺ ዝቅተኛ-በራሪዎችና ማንኛውም ማብሪያ/ማጥፊያ ያላቸው በራሪ መሳሪያዎች  

• የማያሳዩ የቁሻሻ ፌስታሎችና የማያሳዩ ማናቸውም አይነት የፕላስቲክ ፌስታሎች (የሚያሳዩ የቁሻሻ ፌስታሎች ይፈቀዳሉ፡፡) 

• እንስሳት/የቤት (የአካል ጉዳት ያለበትን ሰው ከሚያግዙ እንስሳቶች በስተቀር)  

• ታጣፊ ወንበሮች፣ የካንፕ ወንበሮችና ማንናውም አይነት ጠረጴዛ

• የጠርሙስ መያዣዎች

• ከአንድ ሊትር በላይ የሚይዙ ፈሳሽ መያዣዎች

• የኬሚካል ውህዶች ወይም መርዛማ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ የባዮሎጂ ኤጀንቶች  

• ጋሪዎች

• የጀርባ ቦርሳዎች፣ ሻንጣዎች፣ ተንከባላይ ቦርሳዎች ወይም ይፋዊ ከሆኑ በ NYRR ከተፈቀዱ ቦርሳዎች በስተቀር ያሉ ተመሳሳይ ቦርሳዎች

• Camelbaks® እና ሌላ ማርጠቢያ የጀርባ ቦርሳ (ፈሻስ ቀበታችና በእጅ የሚያዙ የውሀ ጠርሙሶች ይፈቀዳሉ፡፡) 

• ከባድ ሰደርያና በተለይ ውሀ የሚይዙ ባለ ብዙ ኪስ ሰደርያዎች   

• ፊትን የሚሸፍኑና ከሰውነት በላይ የሚረዝሙ አልባሳት (በልክ የሚሆኑ አልባሳት ይቻላሉ፡፡)

• መደገፊያ፣ የባንዲራ ቋሚዎች፣ የስፖርት መሳሪያዎች፣ ወታደራዊና የእሳት አደጋ መሳሪዎች እንዲሁም ከ 11”x17” በላይ ያሉ ምልክቶችን ጨምሮ 

• ፎቶ መነሻ ዘንግና በቀጥታ ከራስ ወይም ሰውነት ጋር ያልተገናኘ ማንናውም የካሜራ መቆሚያ ወይም ማያያዣ  

የውድድሩን ህጎች መጣስ

የውድድሩን ህጎች ሁሉ መጣስ ማለት የሚጠቅሰው የ NYRR ህጎች ኮሚቴን ሲሆን የሚኖሩ ጥሰቶችን በመመልከት ሁሉንም እውነታዎችንና ሁኔታዎች ከግምት በማስገባት መፍትሄ ይሰጣል፡፡

ተሳታፊው ከ NYRR ህጎች ኮሚቴ የጽሁፍ ማስታወሻ ይደርሰዋል፡፡ NYRR ህጎች ኮሚቴ የተለየ ውሳኔ እንደወሰነ የሚያሳይ ማንኛውም መረጃ ማስታወሻው ከተሰጠ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡

ቅጣቶች

የሚከተሉት ቅጣቶች እንደ መመሪያ እንዲያገለግሉ ታስበው የተሰሩ ናቸው፡፡ የህጎች ኮሚቴ ሁሉንም እውነታዎችና ሁኔታዎች ከግምት በማስገባት፣ ተደጋጋሚ ጥፋቶችን ጨምሮ፣ አስፈላጊውን ቅጣቶች ይጥላል፡፡

ሁሉንም የማረጋገጫ ነጥቦች/መቋረጥ፡- ከይፋዊ ውጤቶች ውጭ ሊያደርግ የሚችል ሲሆን ለአንድ ማለትም ከሚኖር የ NYRR ዝግጅት መታገድ ወይም ተከታዩ አመት ዝግጅት መታገድ ሊያስከትል ይችላል፡፡

የመወዳደሪያ ቁጥር ወይም ተለጣፊ ቁጥርን ማስተላለፍ፡- የ NYRR ዝግጅት ውድድር ቁጥርን ወይም ተለጣፊ ቁጥርን ሲሰራ፣ ሲያስመስል፣ ሲቀይር፣ ሲያስተላለፍ፣ ሲገዛ ወይም ሲሸጥ (ወይም አስመስሎ ለመስራት ሲሞክር) ቢገኝ፤ ለሌላ ሰው የራሱን የውድድር ቁጥሩን ወይም ተለጣፊ ቁጥሩን እንዲያደርግ ከፈቀደ ወይም በ NYRR ለራሱ ያልተሰጠውን የውድድር ቁጥር ወይም ተለጣፊ ቁጥር ካደረገ ከውድድር ውጭ የሚደረግና ከ NYRR ዝግጅት ለአንድ አመት መታገድ ወይም የቀጣዩን አመት ዝግጅት መታገድ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ያልተፈቀደ ድጋፍ፡- ማንኛውም የተመዘገበ ተሳታፊ ያልተፈቀደ ድጋፍ ካገኘ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ ይህም የተመዘገቡ ተሳታፊዎች የልተመዘገበ ሯጭ በማንኛውም የዝግጅቱ አካል ላይ እንዲሮጥ መፍቀድን ይጨምራል፡፡

ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ባህሪ፡- NYRR ሩጫ ማእከልን ጨምሮ ከNYRR ዝግጅት በፊት፣ በዛ ግዜና ከዛ በኋላ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ባህሪ ያሳየ ማንኛውም ሰው ከውድድር ውጭ ሊሆን ወይም ወደፊት በሚኖር NYRR ዝግጅት ላይ እንዳይሳተፍ ሊደረግ ይችላል፡፡

የዝግጅቱ አዘጋጆች መመሪያ፡- ማንኛውም የተመዘገበ ተሳታፊ በዝግጅቱ አዘጋጆች መመሪያዎችን ካልተከተለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

ህዝብ በተሰበሰበበት መሽናት/መጸዳዳት፡- ማንኛውም የተመዘገበ ተሳታፊ ህዝብ በተሰበሰበበት ከሸና እና/ወይም ከተጸዳዳ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

ሌሎች ጥፋቶች፡- ከላይ ከተገለጹት ጥፋቶች በተጨማሪ፣ የሕግ ኮሚቴው በውድድር ህጎን ሁሉንም ጠቃሚ እውነታዎችና ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ሌሎች ጥፋቶች ላይ ቅጣት ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡

ከውድድሩ ውጭ የተደረጉ ግለሰቦች ከውድድሩ ውጤት የሚሰረዙና ወደፊት ከሚኖሩ የ NYRR ዝግጅቶችም ሊታገዱ ይችላሉ፡፡ NYRR ማንኛውምንም የመግባት መብትን ሊያግድና ከውድድር ውጭ ሊያድርግ እንዲሁም ከ NYRR ዝግጅቶች ሊያግድ ይችላል፡፡ ይህ ውድቅ ማድረጉ ቀደም ብሎ የተገለጹ ህጎችን መሰረት በማድረግ በእነሱ ብቻ ሳይወሰን የሚጸና ይሆናል፡፡

የአካል ጉዳት ሰለባቸው (“AWD”) ተሳታፊዎች ተጨማሪ ህጎች፡፡

ተጨማሪ የደህንነት ህጎች በእጅ ለሚነዳ ባለሦስት እግር ተሸከርካሪ፡-

ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ የሚጠቀሙ ተሳታፊዎች በሙሉ በተሽከርካሪው ላይ እስካሉ ድረስ የራስ መከላከያ ኮፍያ/ሄልሜት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ የሚጠቀሙ ተሳታፊዎች 5'–6' የሆነ ብርቱካናማ ባንዲራ ተለማጭ በሆነ ዘንግ/እንጨት በተሸከርካሪው ላይ በዝግጅቱ ላይ በሙሉ በሚታይ መልኩ ማሰር አለባቸው፡፡

ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ የሚጠቀሙ ተሳታፊዎች ከቀደመው ተሽከርካሪ ቢያንስ 25 ሜትር መራቅ አለባቸው፡፡

ባለሦስት እግር ተሽከርካሪው ባለ ሞተር ወይም ባለ ፔዳል ከሆነ አይፈቀድም፡፡ ተጨማሪ መሳሪያ፣ መዘወሪያ፣ ወይም በሰንሰለት-ኃይል የሚታገዝ የሳይክል መሳሪያ እንዲሁም በእግር የሚዘወር ዝቅተኛ መቀመጫ ያለው ብስክሌት፣ ባለሦስት እግር ብስክሌት ወይም ባለ ሁለት እግር ብስክሌት በተሳታፊዎች ጥቅም ላይ መዋል አይችልም፡፡

ባለ ሀይል ተሸከርካሪ ወንበር ለሚሳተፉ ተጨማሪ መረጃ፡-

ባለ ሀይል ተሸከርካሪ ወንበር ለሚጠቀሙ ተሳታፊዎች በሙሉ በተሽከርካሪው ላይ እስካሉ ድረስ የራስ መከላከያ ኮፍያ/ሄልሜት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

 

 

Click on a race below to register or view results.
Icon Key
ICON KEY
Completed
Advance Registration
Charity Spots
Near Capacity
Sold Out
Temporarily Closed
Available
Register at Event
In Person
Future Event
Coming Soon
 
TCS New York City Marathon Apply